
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ “ጠንካራ የአመራር ግንባታ ለዉጤታማ የጤና ስርዓት ” በሚል ሀሳብ የመጀመሪያ ዙር የጤናው ዘርፍ የአመራር አቅም ማጎልበቻ ስልጠና በወራቤ ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ ይገኛል ።
በጤናዉ ስርዓት ላይ ያጋጠሙ 15 ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚተገበሩ 12 ስትራቴጂክ መፍትሄዎችን የክልሉ ጤና ቢሮ የፈጠራ እና ስትራቴጂክ ቡድን አጥንቶ ባቀረበው መፍትሄዎች ዉይይት እንደሚደረግ ተገልጿል ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት በጤናው ስርዓት ባለቤትነት፣ ተጠያቂነትና የአመራር ስርዓትን በማሻሻል ዉጤታማ የጤና ስርዓትን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
ዘላቂና በተለያዩ ችግሮች የማይበገር የጤና ስርዓት መፍጠር ይገባል ያሉት አቶ ሳሙኤል የጤናዉን ስርዓት የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ማጠናከር ይገባልም ብለዋል።
በዘንድሮዉ በጀት ዓመት የጤናዉን ሲስተም ዓለም ከደረሰበት ለማድረስ በክልሉ የሚገኙ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎችን ከኤ አይ ጋር አቀናጅቶ ለመስራት መታቀዱን ሀላፊዉ ገልፀዋል ።
በክልሉ የጤና ልማት ስራዎችን ድጂታላይዝ የማድረግ ስራዉ በሆስፒታሎች እየተተገበረ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሀላፊዉ ወረዳዎችን ሙሉ በሙሉ ከወረቀት ነፃ ለማድረግ በአንድ ወረዳ የተጀመረ ሲሆን በሌሎችም ለማስፋት እየተሰራ ስለመሆኑ አመላክተዋል ።
በክልሉ ሀብት የማሰባሰብ ስራ ላይ ህብረተሰቡ በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሀላፊው በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ67 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ የአንድ ሆስፒታል ሙሉ ግብዓት የሚያቀርብ ህዝብ በክልሉ መኖሩን ጠቁመዋል
የክልሉን አጠቃላይ የሰላም ሁኔታ እና ሌሎች የጤና ልማት ስራዎችን ከሌሎች ክልሎች በተሻለ መልኩ ለማረጋገጥ እና የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ሀላፊው አስረድተዋል ።
የክልሉን ህዝብ የጤና እርካታ እንዴት መፍጠር እንደሚቻል፣ከህዝቡ ሀብት እንዴት ማሰባሰብ እንሚቻልና ተግባሮቻችንን እንዴት አቀናጅተን መምራት እንደሚገባ ሰፊ ዉይይት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ይህን ፕሮግራም የተሳካ እንዲሆን ላደረጉ አካላት አቶ ሳሙኤል የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል
ስልጠናዉ ቀጣይ በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ በተመሳሳይ እንደሚሰጥ ከመድረኩ ተገልጿል
በመድረኩ የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ዶ/ር እንጂነር ቶፊቅ ጀማል፣ የጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊዎች እና የማነጅመንት አካላት፣ ከወረዳ የመጡ የጤና አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል ።
በሸምሲያ አደም

