
የሳንኩራ ወረዳ ፣አቶቴ ኡሎ ወረዳ እና የዌራ ዲጆ ወረዳ አስተዳደሮች እና ጤና ጽ/ቤቶች በቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እውቅናና ሽልማት ተቀብለዋል ፡፡
እውቅና እና ሽልማቱን የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች እና ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ከጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እጅ ተቀብለዋል ፡፡
ክልላዊ የ2017 የማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም እና የ2018 ንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር አዳራሽ በድምቀት ተካሂዷል ፡፡

