በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓታችንን በማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ ተመላከተ

  • Post last modified:June 16, 2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከሰኔ 8 እስከ 12 2018 ዓ/ም ድረስ ክልል አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንትን እያከበረ ይገኛል

የጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እለቱን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ስርዓታችንን በማጠናከር የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባ አመላክተዋል

የመድሃኒት አቅርቦት ስርዓት ፣የወረርሽኝ ቅኝትና ምላሽ፣ የላብራቶሪ አገልግሎት ፣ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ እድሳት ጋር ተያይዞ የጤና ተቋማት አገልግሎቶችን ጨምሮሌሎች የጤና ስራዎችን ዲጅታላይዝድ በመደረጉ ህብረተሰቡ ከእንግልት እና ካላስፈላጊ የጊዜ ብክነት በመላቀቅ የመረጃ ጥራት ደህንነት እና ፍጥነት እንዲረጋገጥ ማድረግ መቻሉን አመላክተዋል ።

በክልሉ የመረጃ ጥራትና ተደራሽነት እያደገ መምጣቱን የጠቆሙት ሀላፊዉ
በጥናትና ምርምር የተደገፉ መረጃዎችን በማጠናከር ለዉሳኔ የመጠቀም ባህላችንን ማጎልበት ይገባል ።

ዘመናዊ የመረጃ አስተዳደር ስርዓቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና ቅሬታዎችን በተቀናጀ መልኩ የሚፈታ መሆኑን አቶ ሳሙኤል አክለዋል።

አመራሩ እስከ ታቺኛዉ መዋቅር ድረስ በመዉረድ የባለሙያዉን እምነት፣ የመረጃ አጠቃቀም ፣ክህሎት እና የአመለካከት ችግሮችን በመለየት መረጃን በጥራት እና በተጠያቂነት ለማድረስ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የመረጃ ስርዓቱን ይበልጥ ዉጤታማ ለማድረግ አጋር አካላትና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚስተዋሉትን የመሰረት ልማት ዉስንነቶቾ ለመቅረፍ ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ሳሙኤል ጥሪ አቅርበዋል

በክልሉ የሚገኙ መዋቅሮች በቀጣይ የመረጃ ስርዓትን በተዋረድ እና በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በማስኬድ የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው ሀላፊው አቅጣጫ አስቀምጠዋል ።

ክልል አቀፍ የጤና መረጃ ሳምንትን አስመልክቶ የተዘጋጀ የማስጀመሪያ የዉይይት መድረክ ከሰኔ 8/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ይቀጥላል።

በሸምሲያ አደም