

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በተገኙበት የበጀት ዓመቱ የ11 ወራት አፈጻጸም እንዲሁም በክልሉ በ16 ወረዳ እና 32 ጤና ተቋማት ላይ የተጀመሩ ሞዴል እና ለተሞክሮ ማስፋፊያ የተለዩ የጤና ስራዎች አፈጻጸም የክልል ፣የዞን እና ልዩ ወረዳ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በመጀመሪያ ቀን ውሎው ተገምግሟል ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ባደረጉት ንግግር በቢሮው በሁሉም ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ሕብረተሰቡን ባለቤት በማድረግ በመሰራቱ የመጣ እንደሆነም አስገንዝበዋል።
በየወቅቱ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለይቶ በመቆጣጠር ረገድ የክልሉ ጤና ቢሮ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ሥራ ሰርቷል ሲሉም ተደምጠዋል ኃላፊው።
የተሻሻለው የጤና ፍኖተ ካርታ ትግበራ ያስገኘውን ውጤቶች ለማስቀጠል አጠናክሮ መሄድ ይገባልም ብለዋል ፡፡
በክልሉ ሞዴል እና ለተሞክሮ የሚሆኑ በ16 ወረዳዎች 32 የጤና ተቋማት ለመፍጠር ለአንድ አመት እየተሰራ ያለ ስራ አፈጻጸም በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝ ገልጸው በቀጣይ በየደረጃው ባለቤት አድርጎ ለውጤት ማብቃት ይገባዋል ብለዋል ፡፡
በ11 ወራቱ ግንባታቸው ለተጠናቀቀ ለ18 አጠቃላይ ጤና ኬላዎችና 16 መሠረታዊ ጤና ጤና ኬላዎች የህክምና ግብዓት ተደራሸ መሆኑን የገለጹ ሲሆን የበጀት አመቱን ከዚህ በተሻለ ተግባራት ለማሳካት በቀሪ አንድ ወር በልዩ ትኩረት የሚፈጸሙ ተግባራት እቅድ ተዘጋጅቶ እንዲፈጸም ገልጸው ለወባ እና አገልግሎት አሰጣጥ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥበት አቶ ሳሙኤል አሳስበዋል ፡፡
የጤና ስርዓት ቁጥጥር ከማሻሻል አንጻር፦ በ18,207 ያህል የምግብና ጤናነክ ተቋማት ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ታቅዶ በ18,207 (100%) መደረጉ ተገልጿል
ከወረቀት ነፃ የሆነ የጤና አገልግሎት የተገበሩ ሆስፒታሎች ቁጥርን ከዐ5 ወደ 12 በማሳደግ የታቀደውን ማሳካት የተቻለ ሲሆን ሌሎችም በሂደት ላይ እንደሚገኙ በመድረኩ ተገልጿል ።
መድረኩ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የክልሉ ጤና ቢሮ የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን እና የ2019 የወረዳ ቤዝ ፕላን ዝግጅት ይካሄዳል
አብርሃም ሙጎሮ

