
እንጄንዴር ሄልዝ ኢትዮጵያ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2ኛ ዓመት ማስፋፊያ መርሃ ግብር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሄደ ፡፡
“Integrated RMNCH +PPFP in high case Load Facilities Project” በክልሉ የእናቶች እና የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ እየሰራ ያለ ፕሮጀክት ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ከፍተኛ የወሊድ ጫና ያለባቸው 23 ጤና ተቋማት አዲስ 24 ተቋማት በድምሩ 47 ሲሆኑ በተጨማሪም 23 ዝቅተኛ የወሊድ አገልግሎት የሚሰጡ ጤና ተቋማት ላይ የሚተገብር ይሆናል ፡፡
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች ህጻናት እና አፍላ ወጣቶች ጤናና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሌጂሶ እንደገለጹት በክልሉ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ላይ በተሰራው ስራ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል ፡፡
በክልሉ ከሶስት አመት በፊት የቤተሰብ ምጣኔ ሽፋን 3% ከነበረበት 40% ማድረስ መቻሉን ገልጸው ለዚህም ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ለመጣው ውጤት አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል ፡፡
በክልሉ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ መጨር ያልተጠበቀ እርግዝናን መከላከል ከመቻሉም በላይ የእናቶች እና የሕፃናት ሞትን በመቀነስ ጤናቸው እንዲሻሻል ማድረጉን ገልጸዋል
በእንጄንዴር ሄልዝ ኢትዮጵያ የሲዳማ የደቡብ ኢት/ያ አና የማዕከላዊ ኢት/ያ ክልሎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኦርዶሎ በበኩላቸው በክልሉ ፕሮጀክቱ በክልሉ ከፍተኛ የወሊድ አገልግሎት በሚሰጡ የጤና ተቋማት ላይ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸው በcangaaro mother care ፣ calibrate drip እንዲሁም PPH ላይ በሰራቸው ስራዎች በክልሉ ለበርካታ እናቶች እና ህጻናት ጤና እንዲሻሻል አድርጓል ብለዋል ፡፡
በመድረኩ በፕሮጀክቱ ዝርዝር አፈጻጸም እንዲሁም በቀጣይ እቅድ ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ተጠናቋል ፡፡

