በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የሥራ አፈጻጸም ከባለፈው ዓመት ጋር ስነፃፀር የተሻለ ለውጥ የታየበት መሆኑ ተመላከተ።

  • Post last modified:May 20, 2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ የሥራ ክፍሎች የ2017 በጀት ዓመት የ10 ወራት አፈጻጸም ግምገማና የ2018 እቅድ ዝግጅት መወያያ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሃብቴ ገ/ሚካኤል በዚህ ጊዜ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የሥራ አፈጻጸም ከባለፈው ዓመት ጋር ስነፃፀር የተሻለ ለውጥ የታየበት ነው።በዘርፉ የተሰሩ በርካታ ሥራዎች ለህክምና አገልግሎት ጥራት ልዩ ትኩረትና ቅድሚያ በመስጠት የተከናወኑ መሆኑን ነው አቶ ሃብቴ ያነሱት።ለህብረተሰብ ጤና ተደራሽነት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል ኃላፊው።በቀጣይ ቀሪ ጊዜ የጤና ጣቢያዎች ፌስቲቫል ማዘጋጀትና መረጃን መሠረት ያደረገ ህክምና አገልግሎት ላይ ትኩረት እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል አቶ ሃብቴ።የዘርፉ ቁልፍ አገልግሎት ጠቋሚዎችና የተግባር ሥራዎች፣ የጤና ሀብት ማሰባሰብ ኬዝ ቲም፣ የህክምና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፣ የመድሐኒት እና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ዳይሬክቶሬት እና የክልሉ የደም ባንኮች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርቧል።በዚህም በበጀት ዓመቱ ከመድኃኒትና ከህክምና ግብዓት እጥረት ጋር የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ከመንግስት፣ ከማህበረሰብ፣ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከበጎ ፍቃደኛ ባለሃብቶችና ግላሰቦች ግብዓት የማሳበሰብና የማሰረጨት ስራ መሠራቱ ተመላክቷል፡፡ በህብረተሰቡና ባለሀብቶች ተሳትፎ የተገኘ የብር 100 ሚሊየን በላይ የሚገመት የህክምና መሳሪያዎችና መድኃኒቶች ድጋፍ በተለያዩ የክልሉ መዋቅሮች ለሚገኙ ጤና ተቋማት እገዛ ተደርጓል፡፡ ከኢፌዲሪ ጤና ሚኒስተርና አጋሮች ድጋፍ የተገኘ ግምታዊ ዋጋው 87 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መሳሪያ ለ89 ጤና ተቋማት (64 ጤና ጣቢያዎችና 25 ሆስፒታሎች) በተመደበላቸው መሰረት እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡በበጀት ዓመቱ በክልሉ የኩፍኝ ወረርሽኝ በተከሰተባቸውና ቀውስ በተከሰተባቸው መዋቅሮች ወረርሽኙን ለመከላለልና ለመቆጣጠር እንዲሁም በቀውስ ለተጎዱ ጤና ተቋማት ማጠናከሪያ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ከአጋር ድርጅቶች በማፈላለግ ግምታቸው ብር 10,250,347 የሚሆን የድንገተኛ መድኃኒቶችና ቁሳቁሶች ስርጭት ተከናውኗል፡፡ በክልሉ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም የተግባር ምዕራፍ በክልሉ ስትሪንግ ኮሚቴ በተወሰነው መሰረት የክልሉ የማአጤመ አባላት ምጣኔ 80 ፐርሰንት በማድረስ በተሸለ ደረጃ መፈጸም ተችሏል፡፡በ2017 ዓ ም ከፍተኛ (100%)አፈጻጸም ያስመዘገቡ ወረዳዎች በክልሉ 14 ወረዳዎችን ማፍጠር የታቸለ ሲሆን ስልጤ ዞን 5 ወረዳ፡ጉራጌ ዞን 5 ወረዳ ፤ሀዲያ ዞን 2 ወረዳ፤ሀላባ ዞን 1 ወረዳና ምስራቅ ጉራጌ 1 ወረዳ ናቸው፡፡በተቋማት የጤና ሥርዓት ግንባታ፣ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ተደራሽነት፣ የመረጃ ስርዓት በማዘመን፣ በቅንጅት መሰራት እንደሚገባ ተነስቷል።በውይይቱ ማጠቃለያ በ2017 በጀት ዓመት 10 ወራት ዉስጥ ወሳኝ የሚባሉ ተግባራት ላይ የሚበረታታ ዉጤቶች መመዝገቡ ተነስቶ የታዩ ጉድለቶችን በማረም ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማስፋት በቀሪዉና በቀጣይ በጀት አመት የተሻለ ተግባር ለመፈፀም በቁርጠኝነት ለመሥራት መግባባት ላይ ተደርሷል።በአብርሃም ሙጎሮ