የጤና ሚኒስቴር፣ እና የክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የጋራ የምክክር መድረክ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
መድረኩ የተሰሩ ስራዎች አፈጻፀም የሚገመገሙበት እና ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ 2017 በጤና ዘርፍ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንድንጠነክር ያደረጉ እና ልምድ የተገኘባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 2017 የጤና ፖሊሲዎችን…