የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን መረጃ በፍጥነትና በተደራጀ መልኩ ለመሰብሰብና ለመተንተን የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት ለመዘርጋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።
የ3ኛ ዙር የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች የተጋላጭነት ልየታ አስመልክቶ በዘርፉ ለሚሰሩ ባለሙያዎች በሆሳዕና ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕበረተሰብ ድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም የህብረተሰባችንን ጤና ለመጠበቅና…